Abebech Gobena Charity
አበበች ጎበና ቻሪቲሰኔ 18/2018አዲስ አበባ****የድርጅቱ የሴቶች ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከል ከሰዎች ለሰዎች ሲዊዘርላንድ ጋር በመተባበር ለ3 ወራት በህፃነት ክብካቤ እና ቤት አያያዝ ሲያሰለጥናቸዉ የቆዩ 74 ሴቶችን አስመረቀ፡፡ በመርሃግብሩ የሰዎች ለሰዎች ሲዊዘርላንድ የሃገር ውስጥ ተወካይ አቶ ጌታቸዉ ዘውዱ፤የአበበች ጎበና ቻሪቲ ኤክዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ እሸቱ አረዶ፤የማሰልጠኛ ክፍሉ ሀላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዳምጠው እና የድርጅቱ ሰራተኞች፤ ታዳጊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ማዕከሉ ከተቋቋመ ጀምሮ ለ40ኛ ዙር በተለያዩ መስኮች አሰልጥኖ ለስራ ያበቃ ሲሆን በዚህ በ41ኛ ዙር እያሰለጠናቸዉ ካሉት መካከል በልጅ እና ቤት አያያዝ ሙያ ያስመረቀ ሲሆን በዚሁ ዙር በምግብ ዝግጅት እና የሆቴል መስተንግዶ ሙያ እያሰለጠነ ይገኛል፡፡ ተቋሙ የዘሬዉን ተመራቂዎች ጨምሮ 4017 ወጣት ሴቶችን አስመርቋል፡፡