News and Blogs

የ6ወር የህፃናት ምገባ የመዝጊያ ፕሮግራም ተከናወነ


ታህሳስ 18 ቀን 2017
ለስድስት ወራት ከ4 ወረዳዎች በኑሮ ደረጃቸዉ ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች፤ ለ136 አጥቢ እናቶች እና 150 የአልሚ ምግብ እጥረት ላለባቸዉ ህፃናት በአበበች ጎበና ቻሪቲ እና በሜንሽን ፎር ሜንሽን ሲዊዘርላንድ(Stiftung Menschen für Menschen Schweiz) የጋራ ትብብር ለህፃናት የአልሚ ምግብ ምገባ፤ ለእናቶቻቸዉ ተጨማሪ የምግብ ዱቄት፤ ዘይት እና የንጽህና መጠበቅያ ሳሙና በመስጠት ይደረግ የነበረው ድጋፍ ዛሬ ታህሳስ 18/2017 በስኬት ተጠናቀቀ።

በመዝጊያ መርሃ-ግብሩ ላይ የአበበች ጎበና ቻሪቲ ኤክዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ እሸቱ አረዶ የመሸኛ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተጠቃሚዎችም በኩል ምስጋና ቀርቧል።

ይሄዉም አገልግሎት በቀጣይ ስድስት ተከታታይ ወራት ለአዳዲስ ተመዝጋቢዎች የሚሰጥ  ይሆናል።

Telegram
Scroll to Top